ዮሐንስ ሞላ

ዮሐንስ

ዮሐንስ ሞላ ከመደበኛ የዳታቤዝ ዴቨሎፐርነት ሙያው በተጨማሪ፣ ገጣሚ እና ጸሀፊ፣ እንዲሁም የዘፈን ግጥም ደራሲ ነው። ከጸሃፊነት ችሎታው ጋር ተያይዞ የጉማ አዋርድን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀብሎ ያውቃል። የመጀመሪያ ዲግሪውን ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በስታቲስቲክስ፣ የሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስነ ሕዝብ ጥናት (Population Studies) አግኝቷል። ከዚህ ቀደም ለብቻው ያሳተማቸው “የብርሃን ልክፍት”፣ “የብርሃን ሰበዞች” እና “በከንፈርሽ በራ’ፍ” የተሰኙ ሦስት የግጥም መጽሐፍት፣ እንዲሁም ከሮማንያውያን እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ በመሆን “የቅኔ መስተጋብር” (Poetic Encounter) የተሰኘ መጽሐፍ አሳትሟል። ዮሐንስ ከሙያ እና ስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ በተጨማሪ በማህበረሰብ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ጊዜውን እና እውቀቱን ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት ያውላል። Hubrizon የተባለ የአይቲ ኩባንያን በተባባሪነት መስርቷል። ከዚህ በፊት ይተላለፍ የነበረ “ጠይም በረንዳ” ፖድካስት ( ኢትዮቴዮ ጠይም ) እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ጥበባት ማህበር ከመስራቾች መካከል አንዱ ነው።

Books by ዮሐንስ: