አለምነህ ደሴ

አለምነህ

ዓለምነህ ደሴ ሙላው 1939 ዓ.ም በቀድሞው ቤጌምድርና ሰሜን ጠቅላይ ግዛት ተወለደከአባቱ ከአቶ ደሴ ሙላው ተሰማ እና ከእናቱ ወ/ሮ የዛብ ንጉሴ ተወለደ በተለወደ በሁለት ወር ሣይሞላ ወላጅ እናቱ ወጣት የዛብ ንጉሴ በጠና ታማ ከዚህ ዓለም በመለየቷ የዓለምነህ እጣ ፋንታ በአያቱ በወ/ሮ ጠየቁ ካሣ እጅ መውደቁ ሆነ ወ/ሮ ጠየቁም በወቅቱ ጥሩ ባለፀጋ በመሆናቸው ብዙም አልተጐዳም የእናት ጡት ባያገኝም የላም ወተት አልስማማ ቢልም በፍየል ወተት በአስቸጋሪ ሁኔታ የፍየል ወተት እየተመገበ አደገ የአስር ዓመት ልጅ እንደሆነ በእንክብካቤ ያሳደጉትን አያቱ በሞት ተለዩበት ከዚህ በኋላ የእናቱ ትልቅ እህት የሆኑት ወ/ሮ ስራየ ንጉሴ ኃላፊነቱን በመውሰድ በውነቱ ከእናት ባላነሰ እክብካባቤ አሣድገውታል፡፡የዓለመነህ ወደ ከተማ ማሰብ እንዴት ተጀመረ በወቅቱ ጉብጉብ የአስኳላ ትምህርት ሲከፈት ሁሉም ልጁን ሲያስመዘግብ ለማስተማር ዓለምነህን ለማስተማር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አክሰቱን ወ/ሮ ስራየን ንጉሴን እንዲያስተምሩት ሲጠይቅም ፈቃደኛ አልሆኑለትም፡፡ ወ/ሮ ስራየም እንድ ልጅ ብቻ ስላለት ዓለምነህን ገበሬ እንዲሆንላቸው ነው የፈለጉት በቅንነት እንጅ በክፋት አልነበረም፡፡ 1 ሰው ከማጣት የተነሣ ነው የሚመለስለው ከዛም የዓለምነህ ደሴ እጣ ፋንታ ወደ አዲስ አበባ ነበር ህልሙ፤ ህልሙን እውን ለማድረግ ጓደኛ አፈላልጎ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ጀመረ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ገባ ከዛም ከአንድ አመት እንግልት በኋላ በ1963 አዲስ አበባ ባንክ በተራ ሰራተኝነት ተቀጠረ ከዛም 12 ዓመት ካገለገለ በኋላ የደርግ መንግስት ሲመጣ በካድሬነት ስልጠና የካቲት ፓለቲካ ት/ቤት ኮርስ ሰልጥና ገብቶ የስድስት ወር ስልጠና ጥሩ ውጤት በማምጣቱ ወደ ፓርቲው ኮምሽን ኢሠፓአኮ ተመደቦ በኃላፊነት ከዚያም ኢሠፓ ሲመሰረት በዛው ቀጥሎ እስከ 1983 ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ ለ16 ዓመት ከስድስት ወር በስር ቆይቶ ተፈቷል፡፡ በስር በነበረበት ጊዜ በህግና በንብረት አስተዳደር ትምህርት የቀሰመ ሲሆን ከስር ከተፈታም በኋላ በተለያዩ መ/ቤቶች ባለው ችሎታ መሰረት አገልግሏል፡፡በስር በነበረበት ጊዜ ሠስት መጻሕፎችን ጽፏል ከነዚህም ወደቆ የተገኘው ዶ/ር፤ ስራ ለሰሪው አሾህለጣረው፤ የክፉ ሰዎች እጣ የሚሉ ሲሆኑ ለሕትመት የበቃው ወድቆየተገኘው ዶ/ር ብቻ ነው፡፡ ከ300 ገፅ በላይ ግጥሞች ሲኖሩት አንዱን መለስ ብየ ሳየው የሚለው በጦቢያ መጽሔት ታትሞ ወጥቷል፡፡ በአጠቃላይ በሕይወት ውጣውረድን እንደትምህርት የተጠቀመበት ሰው ነው፡፡ ዓለምነህ ደሴ ሙላው

Books by አለምነህ: