ዘዌ

ዘዌ

Author/s: ዝጋለ አያሌው

Subjects

Sociology, Spiritual, Religion, Non Fiction

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

አዚች ሀገር ላይ ሁል ጊዜም ግርም የሚለኝ አጥፊዎቿና ጠፊዎቿ በትክክል ሳይረዷት ማለፋቸዉ ነው።ሀገራችን 7000 አመት ሙሉ ጦርነት ሲያካሂዱባት አንድም ጊዜ እጅ እንዳልሰጠች ቢታወቅም ቆይ ይህን ሁሉ ጦርነት የሚያዉጁብን እኛ ማናውቀዉ እነሱ የሚያዉቁት ምን ነገር አለ? ብሎ የጠየቀ ማን ይኖር ይሆን ? እረፍት ስለተሰጠን ጦርነት የቆመ የሚመስላቸው ሰዎች ለራሳቸው የማስተባበያ ተስፋ የሚሰጡ ናቸው ። በእርግጥ በኢትዮጵያ ላይ የተያዙ አጀንዳዎችን ያልተረዱ ሰዎች ከዚህ በላይ ምን ሊያስቡ ይችላሉ ? ቆይ ይህ ሁሉ ምስጢር እዚች ሀገር ታጭዶ ይፋ ይውጣ እንጂ ሲባል ተው ጊዜው አይደለም ተረጋጉ ለዘራፊዎች አጋልጣችሁ አትስጡ ማለት የተለመደ ነው ።ነገር ግን በዚህ ዘመን የሚደባበቅ ጉዳይ አይኖርም ። በዘዌ ውስጥም በርካታ የተደበቁ ምስጢራት ገሀድ ወጥተዋል ። እውነታውን ሳናውቅ ከምናልቅ እውነታውን አውቀን መክፈል ያለብንን መስዋዕት እንከፍል ዘንድ ግድ ነው ። በጥቅሉ ቅድስት ድንግል ማርያም ኢትዮጵያዊ ናትን ? ዝዋርያስ የካም ? ወይስ ያፌት ? ካህኑ መልከ ጼዴቅ አብራምን የባረከው ኢትዮጵያ ውስጥ ነውን ? አዋሽ የስነ ፍጥረቱ ኤፌሶን ነውን ? አዋሽ ኢትዮጵያን ሳይሻገር ለምን ቆመ ? ወደፊትስ ይሄዳል ? እኛ የማናውቀው ጠላቶቻችን የሚያውቁት ምን ሀብት ይኖር ይሆን ? የአለም ሀገራትስ ኢትዮጵያን ብቻ ጦርነት የሚያፈራርቁባት ጥልቅ ምስጢር ምንድነው ነው ? ኢትዮጵያ ውስጥ እነዚህ ስሞች እንዴት ተገኙ ? አንፆኪያ ኤፍራታ ጌቴሴማኒ ደብረዘይት ናዝሬት ቆፕሮስ ዮርዳኖስ ጽዮን ቤተልሔም ቀራንዮ ኦፊር ኤውላጥ ተርሴስ ራማ ደብረ ታቦር ኮሬብ ደብረሲና ተራራ እሺ እስራኤል ሀገር ግዮን የሚባል ወንዝ አለ። ኮረጁን ወይስ ተኮረጅን ? ማንኛውም ዜጋ ሀገሩን ለማወቅ የሚፈልግ ትውልድ ይህን መፅሐፍ ቢያነበውና ቢያስነብበው ከብዙ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቀውሶች ራሱን ይታደጋል ። ለቀጣይ ምርምር መነሻም ይሆነዋል የሚል እምነት አለኝ ። ደራሲው ።

0.0 (0 reviews)