ብርሃኔ ሩቢ
Summary
ብርሃኔ ሩቢ የፀሀፊዋ እዉነተኛ ግለ ታሪክ ነዉ። ያለእድሜ ጋብቻን ለማምለጥ በሚደረግ ትንቅንቅ የሚገጥማትን አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳቶች ችግሮቿን ለማለፍ የምትጠቀምበትን የመፍትሔ መንገድ እንዲሁም ሴቶች የሚጫንባቸውን ከባቢያዊ አጉል ልማዶች እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየን ነዉ። ታሪኩ ታሪካዊ ቦታ ከሆነው መቅደላ አምባ ተነስቶ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ይዘዋወራል። በርካታ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ይዘልቃል። ብዙ የረሃብ ቀናትን ያስቃኘናል። አፍኝ ሳቅን ያስቅመናል። ከተወዛዋዥነት እስከ ቤት ሰራተኝነት ከአስተናጋጅነት እስከ ፋይናንስ ተቋማት ሰራተኝነት የስራ ቦታዎችን ያስመለክተናል። ገና በጠዋቱ ለፈተና የታጩትን ሁሉ ለማበርታት መቀነት መሆን የሚችል ግለ ታሪክ ነዉ።